Mols.gov.et

በበጀት ዓመቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተቀመጠውን ሰፊ ዕቅድ ለማሳካት ያሉ ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር መሰራት እንዳለበት ተገለፀ።

ህዳር 4, 2024
በበጀት ዓመቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተቀመጠውን ሰፊ ዕቅድ ለማሳካት ያሉ ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር መሰራት እንዳለበት ተገለፀ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እያካሂዷል፡፡ በውይይቱ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻን ጨምሮ የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተቀመጠውን ሰፊ ዕቅድ ለማሳካት ያሉ ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ታሳቢ በማድረግ መድረኩ እንደተፈጠረ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ተሻለ በሬቻ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል፡፡ በበጀት አመቱ ያስቀመጥነው ግብ ትልቅ እንደመሆኑ የአገር በቀል ዕውቀቶችና ክህሎቶችን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ በማልማት፣ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ለማሳካት ከእሴት ሰንሰለት በመነሣት የሙያ ደረጃዎችን የማሻሻል ሥራዎች መሰራታቸውን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም የሩብ ዓመቱን ግምገማ ከ11 የዲ ኤን ኤ እና ከሶስቱ አበይት አንኳር የሥራ ተግባራት አንጻር ቁጥሮችን በማናበብ ግብረ መልስ መሰጠት አለበት ብለዋል ፡፡ በቀጣይ በግምገማችን እንደችግር የተነሱ እና አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የሆኑት ላይ የማካካሻ ዕቅድ በማዘጋጀት በፍጥነት ወደ ሥራ ይገባል፡፡ እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ የግንኙነት አግባብ መሻሻል እንዳለብት አንስተው የሠራተኛው የመረጃ ልውውጥን ማሳደግ፣ የሪፎርም ሥራዎችን እንዲሁም አበይት ተግባራት ላይ በፖሊሲ፣ በአይ ሶ ስታንዳርድ ፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በመመሪያዎች ፣በመምህራን ልማት እና የሥልጠና ጥራት ላይ በቀጣይ ትኩርት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡
amAM
Scroll to Top