Mols.gov.et

ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ

ጥቅምት 22, 2024
ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡ ክብርት ሚኒስትር ይህን የገለፁት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዘርፉን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በተገመገመበት መድረክ ላይ ነው፡፡ ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በበጀት ዓመቱ እንደ ዘርፍ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት የተቀናጀና የተናበበ ርብርብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ መሰረት ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሰው ሀይል ዝግጅት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡ እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራ ግብዓትና ግብይት መስኩ ላይ ለበርካቶች ሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚቻል የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በየደረጃው ያለውን ፀጋ መሰረት ያደረገ እና ያለውን ፍላጎት ያማከለ ሥራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
amAM
Scroll to Top