Mols.gov.et

bini

ዜና

የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ የግሉ ዘርፍ፣ መሠረተ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሰለሞን ኩይኖር ከተመራው የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ በግብርናው ዘርፍ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር ለዜጎች ሰፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በኢትዮጵያና በአፍሪካ የልማት ፈንድ መካከል በተፈረመው ስምምነት መሰረት የተከናወኑ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ መመልከታቸውንና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም ማስቀመጣቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ልማት ባንክ የግሉ ዘርፍ፣ መሠረተ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ሰለሞን ኩይኖር እና የልዑካን ቡድን አባላት ለስምምነቱ ተግባራዊነት እያደረጉ ላለው ጠንካራ ድጋፍና ክትትልም አመስግነዋል፡፡

Read More »
ዜና

በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ የክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የክህሎት መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የተፈረመው ስምምነት በፍጥነት ወደ ትግበራ የሚሸጋገርበትን ሁኔታ በዝርዝር መመልከታቸውንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ስለማስቀመጣቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል ፡፡
በቅርቡ የተፈረመው ይህ ስምምነት በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ዘርፉ በርካታ ሴቶችንና ወጣቶችን የሙያ ባለቤት በማድረግ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአፍሪካ በአይነቱ ልዩ የሆነውን የክህሎት ፓርክ በመገንባት ኢትዮጵያ ለያዘችው ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዞ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡
የጣሊያን ኤምባሲ ምክትል ልዕክ ኃላፊ ክቡር ሉካ ካርፒንቲየሪ፣ የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሚሼል ሞራና እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ስምምነቱን ወደ ተግባር እንዲሸጋገር እያደረጉ ላለው ያለሰለሰ ጥረትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Read More »
ዜና

ሥራው ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ፀጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሥራው ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ፀጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ውስጥ ከሚካተቱ አገልግሎቶች መካከል የቨርቹዋል የኢንተርፕራይዝ ምስረታ አገልግሎት ይገኝበታል።
ይህ አገልግሎት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስርዓቱ ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ጸጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሥራው ሀገራዊ የመረጃ ስርዓትን ዘመኑን በሚዋጅ አሰራር የሚያዘምን ከመሆኑም ባሻገር ኢንተርፕራይዞች በአካባቢ ሳይወሰኑ የገበያ ድጋፍ እንዲያገኙ፣ አካታች የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና ጸጋቸውን ማዕከል ያደረገ ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል ሆኖ መበልፀጉን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ጠንካራና ተወዳዳሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ለማፍራት ዜጎችን በሥርዓቱ የመመዝገብ እና እንዲደራጁ የማድረግ ሥራ በልዩ ንቅናቄ እና በትኩረት እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡

Read More »
ዜና

ቀጣናዊ ትስስር በክህሎት ልማት …

ቀጣናዊ ትስስር በክህሎት ልማት …
የክህሎት ልማት ሥትራቴጂና አቅጣጫችን ከሀገራዊ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና አቅጣጫዎች ጋር እንዲሰናሰል ተደርጎ የተቃኘ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ከሀገራዊው ባሻገር ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ቀጣናዊ የሙያ ብቃት ማዕቀፍ ተዘጃቶ ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡
በዚህም ዜጎች ተንቀሳቅሰው የመስራት ብቻ ሳይሆን የመሰልጠን መብታቸው እንዲከበር ለማድረግ ትልቅ ሥራ ተሰርቷል፡፡
ይህ በመሆኑም የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በሀገራችን በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለቀጣናው ሀገራት ዜጎች የስልጠና ዕድል በመስጠት ብዙዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም ሰሞኑን በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የሶማሊ ላንድ ዜጎችን አስመርቋል፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ ቢሮው ከከተማው ባሻገር የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮትን በትምህርትና ስልጠናው መስክ የማዋሃድ ሥራን በልዩ ትኩረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
በዚህም 45 የሚሆኑ የሶማሊ ላንድ ዜጎችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ለምረቃ ማብቃቱን ገልፀው በቀጣይም ሌሎች የቀጣናው ሀገራትን ዜጎች የሥልጠና ዕድል በመስጠት ቀጣናውን በትምህርትና ስልጠና የማስተሳሰር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የድሬዳዋና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሠለሃዲን አብዱልሃሚድ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ቀጣናውን በትምህርትና ስልጠና ለማዋሃድ በንቃት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ስልጠናቸውን አጠናቀው ለምረቃ የበቁተት የሶማሌ ላንድ ዜጎች የህዝቦች ወንድማማችነት ማሳያ ናችሁ ብለዋል፡፡

Read More »
ዜና

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ…

ፖሊሲውን ተከትለው እየተዘጋጁ የሚገኙት የህግ ማዕቀፎች ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተቃኙ ናቸወ፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ እና ፖሊሲውን ተከትለው ተግባራዊ በሚደረጉ የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የየክልሉ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እና የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፤ በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀውን የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ እና ፓሊሲውን ተከትለው እየተዘጋጁ የሚገኙት የህግ ማዕቀፎች ሚኒስቴሩ የጀመረውን የዘርፉ የለውጥ እሳቤ ላይ ያተኮሩ እና ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ማሳካት በሚያስችል መልኩ የተቃኙ ናቸው፡፡
የሥራ አጥነት ችግር መቅረፍ የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እነዚህ ፓሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች በዘርፉ የሚታዩ የአተገባበር ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
በመድረኩ አዲሱ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ እና ፖሊሲውን ተከትሎ የሚወጡ የሕግ ማዕቀፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

Read More »
ዜና

ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ በመክሊቱ ስልጠና ማግኘት የሚችልበት ማዕከል ይሆናል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ በመክሊቱ ስልጠና ማግኘት የሚችልበት ማዕከል ይሆናል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል የሚሆን ‹‹የ21ኛው ክፍለዘመን ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት›› ግንባታ አስጀመረ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢንስቲትዩቱ የሚያስገነባውን የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ግንባታውን ሲያስጀምሩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ ትምህርት ቤቱ እያንዳንዱ ተማሪ በመክሊቱ ስልጠና ማግኘት የሚችልበት ማዕከል ይሆናል ብለዋል፡፡
በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፓሊሲ ላይ የተቀመጠውን የትምርት ስርዓቱን ቮኬሽናላይዝ የማድረግ ግብ ለማሳካት ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ መሠል ተቋማትን መገንባት ይገኝበታል ብለዋል፡፡
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር በበኩላቸው የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት የክህሎት ማሳደጊያ ቦታ እንዲሆን ታስቦ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
የመጀመሪያ ዙር ግንባታ የህጻናት መጫወቻን ጨምሮ በ1 ሺ 6 መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚሰራ ሲሆን ከሁለት ወራት በኋላ ተጠናቆ ለስራ ዝግጁ እንደሚሆን ግንባታውን የጀመረው የግንባታ ተቋራጭ ገልጿል::

Read More »
ዜና

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
የሥልጠና ተቋማቱ ዜጎች ሀብት የሚፈጥር የሥራ ሃሳብ አመንጪ እና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ መሆኑን ተናግረዋል።
ክብርት ሚኒስትር ለኢዜአ እንዳሉት የክህሎት ልማት በማጎልበት ለኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂነትና ስራ አጥነት ቅነሳ አስፈላጊ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ለክህሎት ልማት ደግሞ የስልጠና ተቋማትን የማመዘን፣ መሠረተ ልማት ማሟላትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማከናወን ይጠይቃል ብለዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
በዚህም ተቋማቱ የሚያወጧቸውን ተማሪዎች ሀብት ፈጣሪ የሥራ ሃሳብ አመንጪና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የቴክኒክና የሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በዚህ ቅኝት እንዲሰሩና ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ዝንባሌና መክሊት ያላቸው ዜጎች በማዕከላቱ ሥራ መፍጠር እንዲችሉ እንደሚያደርግ ክብርት ሚኒስትር መግለፃቸው ጠቁሞ የዘገበው ኢኤአ ነው፡፡

Read More »
ዜና

ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ፡፡
ክብርት ሚኒስትር ይህን ያስታወቁት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡
የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ስርዓቱ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ በስርዓቱ ላይ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ፈፃሚዎች እንዲሁም ተጠቃሚዎች ግልጽነት እንዲኖራቸው እየተደረገ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መንግስት ከመንግስት፣ መንግስት ከኩባንያ እና ኩባንያ ከኩባንያ ጋር በሚያደርጉት ስምምነት ሊተገበር እንደሚችል ያነሱት ክብርት ሚኒስትር አልፎ አልፎ በግል ጥረት የሚገኙ የሥራ ዕድሎችንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጋዊ በሆነ መንገድ ሥምሪት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ሆኖም በየትኛውም አማራጭ ቢሆን ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ እንደሆነም በአንክሮት አንስተዋል፡፡
የሁለትዮሽ ስምምነት ከተደረሰባቸው ሀገራት ውጪ ዜጎችን ለሥራ እንልካለን የሚሉ አጭበርባሪዎች መኖራቸውን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር ህብረተሰቡ እራሱን ከእነዚህ አካላት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡

Read More »
ዜና

በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠት ስርዓቱ ይበልጥ አካታች እንዲሆን የሚያስችል ነው፡፡ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠት ስርዓቱ ይበልጥ አካታች እንዲሆን የሚያስችል ነው፡፡
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠት የዜጎችን ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ስርዓቱ አካታች እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተጠቆመ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ አንደገለጹት በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊን በላይ ዜጎች በመደበኛ ስልጠና ተደራሽ ይሆናሉ፡፡
በገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናም ከሦስት ሚሊየን በላይ ዜጎች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ የሥራ ገበያውን ይቀላቀላሉ፡፡
በአንፃሩ በርካታ ዜጎች ከመደበኛ ስልጠና ውጪ ባገኙት ሙያ የሥራ ገበያ ውስጥ ገብተው ይሰራሉ፣ ኢኮኖሚውንም በእጅጉ ይደግፋሉ፡፡
ነገር ግን በዚህ መልክ የሚገኝ እውቀትና ክህሎትን የሚያስተናግድ ስርዓት እስከ ቅርብ ጊዜ ስላልነበረን በልምድ የሙያ ባለቤት የሆኑ ዜጎች ተወዳዳሪነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን በተገቢው ልክ ማሳደግ አይችሉን ነበር ብለዋል፡፡
ይህን ከግምት በማስገባትና የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ ሚኒስቴሩ በልምድ የተገኘ ሙያን በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱን አመላክተዋል፡፡
በርካታ ዜጎች በልምድ ያገኙትን ሙያ በመጠቀም በተለያዩ ዘርፎች በሥራ ላይ እንዳሉ ያመላከቱት ዶ/ር ተሻለ የኮንስትራክሽን፣ የቱሪዝምና የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪውን በማሳያነት አንስተዋል፡፡
የተዘረጋው ስርዓት ይህን የሰው ሃይል ብቃቱን፣ ተወዳዳሪነቱ እና ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ወሳኝ ሚናም እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
የሥራ ጥራትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የሰው ሃይሉን ምርታማነት ለማሳደግ ሚናው ከፍተኛም እንደሆነ ነው ዶ/ር ተሻለ ያመላከቱት፡፡
የተሻሻለ ሀገራዊ የሠራተኛ ፕሮፋይል እንዲኖረን፣ ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር፣ የዕድሜ ልክ ትምህርትን ከማበረታታት እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪው መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲፈጠር ከማድረግ አኳያ የተዘረጋው ስርዓት ሚናው የላቀ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
ለሥርዓቱ ውጤታማነትም የዘርፉ ተዋንያኖች በሙሉ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉም ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

Read More »
ዜና

በፍጥነት ሊያሻግረን የሚችለው በአስተሳሰብ ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ስንችል ነው፡፡ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ

በፍጥነት ሊያሻግረን የሚችለው በአስተሳሰብ ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ስንችል ነው፡፡
የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚኒስቴሩ የሪፎርም አጀንዳዎች ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረውን ውይይት አጠናቋል፡፡
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እንደገለጹት፣ በሚኒስቴሩ ተቀርፀው ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎች አበረታች ውጤት እያመጡ ነው፡፡
በዘርፉ በአዲስ ይዘትና አቀራረብ በኢንተርፕሪነርሺፕ ላይ እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች በዘርፉ እየመጣ ላለው ውጤት ሚናቸው የላቀ ነው፡፡
የአመራሩና የሠራተኛውን አስተሳሰብ በመቀየር ብቻ የውስጥ ገቢያቸው በብዙ እጥፍ ያሳደጉ ተቋማት መኖራቸው ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር በፍጥነት ሊያሻግረን የሚችለው በአስተሳሰብ ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ስን ችል ነው ያሉት የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ሚኒስቴሩ እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ፀጋዎች አሟጦ ለመጠቀም አስተሳሰብ ላይ የሚሠራው ሥራ ወሳኝ መሆኑን በአንክሮ ገልፀዋል ፡፡
ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑ ተቁማት አንዱ በሆነው አንተርፕር ነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አማካኝነት የተጀመረው ሥራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው መድረኩ የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ሥራቸውን በእጅጉ የሚያግዝ እንደሆነ ጠቁመው የተጀመሩ ውጤታማ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው መቀ ጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
amAM
Scroll to Top