Mols.gov.et

የአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

Mr. DANIEL TERESSA SHONE

የህይወት ታሪክ

አቶ አሰግድ ጌታቸው ይመኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጂኦግራፊና ኢንቫሮሜንታል ስተዲስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪያቸውን በተቋማዊ አመራር አሜሪካን አገር ከሚገኘው አሱዛ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

አሁን ወዳሉበት የሥራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ላይ ሰርተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽህፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን በዋና ስራ አስኪያጅነት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በምክትል ሥራ አስኪያጅነት መርተዋል፡፡

amAM
Scroll to Top