Mols.gov.et

የተቀናጀና ስልታዊ ተግባቦት፤ ለግቦቻችን ስኬት…

ታህሳስ 30, 2023
የተቀናጀና ስልታዊ ተግባቦት፤ ለግቦቻችን ስኬት…. እንደ ዘርፍ ለለየናቸው ግቦች ስኬት የተቀናጀና ስልታዊ የተግባቦት ሥራዎችን ማከናወን በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ከኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እና የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይታችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተሰጠው ተልዕኮ አኳያ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም አሠሪና ሠራተኞች ግንኙነት እና ከተቋም ግንባታ አንፃር የለየናቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች እና እንዲያሳኩ የታሰቡትን ግቦችን ተመልክተናል፡፡ በየደረጃው ጠንካራ፣ የተቀናጀና ስልታዊ የተግባቦት ሥራ መስራት ለግቦቹ ስኬት ወሳኝ እንደሆነም የተግባባን ሲሆን በቀጣይም ዝርዝር የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት ለይተን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በምናደርግበት ሁኔታ ላይ መክረናል፡፡ የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እና የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ ለሰጣችሁን ጊዜ እና እሴት አካይ ግብዓት እንዲሁም ለሥራው ስኬት ላሳያችሁን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!
amAM
Scroll to Top