Mols.gov.et

የሥራ ፈጠራ ውድድር

ሐምሌ 8, 2022

የሥራ ፈጠራ ውድድር የሁለተኛ ዙር #አሁን የዲጂታል አንተርፕነሮች የሀሳብ ማበልፀጊያ ፕሮግራም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አጋዥነት በመጀመሪያ ዙር አካሂዶት አሸናፊዎችን ለሥራ ያበቃው የዲጂታል አንተርፕርነሮች #አሁን ሁለተኛ ዙር የሥራ ፈጠራ ውድድር በይፋ ተጀምሯል፡፡ ፕሮግራሙ የ4 ወር የሀሳብ ማበልፀጊያ ድጋፍና የሥራ ማስጀመሪያ ሽልማት ያካትታል፡፡ አዳዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የዲጂታል የሥራ ሃሳብ ያላችሁ አመልካቾች በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ። የማመልከቻ ቅጹን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡ https://enkopa.org/high-growth/ አለያም በመልዕክት ሳጥን ቁጥራችን 25534 ቅፁን ሞልቶ መላክ ይቻላል፡፡ ምዝገባው የሚጠናቀቅበት ጊዜ፦ ሐምሌ 24, 2014 ዓ/ም

amAM
Scroll to Top