Mols.gov.et

ማብቃት ላይ ያተኮረ ድጋፍና ክትትል…

ጥር 6, 2026
ማብቃት ላይ ያተኮረ ድጋፍና ክትትል የሥራና ክህሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሄደውን ድጋፍና ክትትል እና የመስክ ምልከታ አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ በሥራው ለሚሳተፉ አካላት ኦረንቴሽን ሰጥተዋል፡፡ የመስክ ምልከታው ሚኒስቴሩ በዘርፉ የቀረጻቸው እሳቤዎች አተገባበር፣ ከአፈጻጸም አኳያ ወደኋላ የቀሩትን መደገፍ፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ሪፎርም ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም በክህሎት ልማት፣ በሥራ ሥምሪት፣ በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍና በተቋም ግንባታ ዘርፎች የተገኙ ልምዶች እና ተሞክሮዎች ቀምሮ ለማስፋት ያስችላል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም በበጀት አመቱ የተያዙ ትላልቅ ግቦችን ለማሳካት የተደረገው ዝግጅትና በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች የምልከታው አካል እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ ድጋፍና ክትትሉ ከጥር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን በሂደቱ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች የመቀመርና የማስፋት ስራም እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
amAM
Scroll to Top