Mols.gov.et

“ብሩህ አዕምሮዎች የተፍታቱ እጆችና በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ክላስተር…

ሚያዝያ 16, 2025
“ብሩህ አዕምሮዎች የተፍታቱ እጆችና በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ክላስተር በኮሌጆች የሚደረገው የቴክኖሎጂ ክህሎትና ተግባራዊ ጥናትና ምርመር ውድድር እንዲሁም አውደ ራዕይ መካሄድ ጀምሯል ። የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ል ሀላፊና የሙያ ስልጠናና የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍስሀ ፍቾላ አንደገለፁት፤ በዘርፉ በተደረገው ሪፎርምና ኮሌጆቹ የአከባቢውን ፀጋ መሠረት ያደረገ ስልጠና እንዲሰጡ በተደረገው ሥራ ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል። የህንፃ ግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ኮሌጆችን ለማጠናቀቅና ጥራት ያለውን ሥልጠና ለመስጠት በተደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤት መታየት ጀምሯል ብለዋል፡፡ በ2015 በተካሄደው ሀገር አቀፍ ውድድር ክልሉ አመርቂ ውጤት እንዳገኘ አመላክተው ዘንድሮም ይህን ውጤት ለማስጠበቅ በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆንን ገልጸዋል፡፡ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ ባራሣ በበኩላቸው በሀዋሳ ክላስተር አራቱም ኮሌጆች( ሀዋሳ ፖሊ፣ ሀዋሳ ቴግረ_ዕድ ፖሊ፣ ቦሪቻ እና ቱላ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች) በ20 ሙያዎች ለመሳተፍ በቂ ዝግጅት መደረጉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
amAM
Scroll to Top