Mols.gov.et

ፈጠራ የታከለበት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት…

ህዳር 4, 2024
ፈጠራ የታከለበት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት… የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓትን ጨምሮ ዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት በማበልፀግና ወደ ሥራ በማስገባት ተስፋ ሰጪና ተጨባጭ ውጤቶችን ለማዝመዝገብ ተችሏል፡፡ ከቴክኖሎጂ አማረጭ ጎን ለጎን በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ፈጠራ በታከለበት የአሰራር ስርዓት ለመፍታት ሚኒስቴሩ ከሚተገብረው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ጎን ለጎን የ ‹‹ Public Sector Innovation Lab ›› ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩ የጀመረውን የፐብሊክ ሴክተር ኢኖቬሽን ላብ ማጠናከር የሚያስችል ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ ባስተላለፉት መልዕክት ፐብሊክ ሴክተር ኢኖቬሽን ላብ ሚኒስቴሩ የተሰጠውን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ተጨማሪ አቅም ይሆነዋል፡፡ በዚህ ላብራቶሪ በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ ሃሳቦች ይፈልቃሉ፣ ችግሮች ተለይተው የመፍትሔ ሀሳቦች ይቀርቡበታል፣ የምርምር እና የትግበራ ሥራዎች ይከናወኑበታል ብለዋል፡፡
amAM
Scroll to Top