Mols.gov.et

የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር …

ነሐሴ 5, 2026
የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችል አቅም መፍጠርን ያለመ ስልጠና የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራና ክህሎት ቢሮ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በጣልያን ፕሮጀክትና በሴቭ ዘ ችልድረን የፋይናንስ ድጋፍ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና በዘርፉ አዲስ እሳቤ፣ በባዮሜትርክስ ምዝገባና በዕቅድና ሪፖርት ዝግጅት ላይ ያተኩራል፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአፋር ክልል፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ኢብራሂም ስልጠናው በዋነኛነት በየእርከኑ የሚገኙ አመራርና ባለሙያዎች የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችላቸውን አቅም ለማጎልበት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በሚገኙ 30 የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊዎች የባዮ ሜትሪክስ ምዝገባ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ቢሮ ኃላፊው የምዝገባ ሂደቱን በሚጠበቀው ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ዕውቀትን ቢሮው ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ በሥራና ክህሎት ዘርፍ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉ ከዕቅድ ዝግጅት የሚጀምሩ እንደመሆናቸው ‹‹አንድ ዕቅድ፣ አንድ ሪፖርት›› የሚለውን የሚኒስቴር መ/ቤቱን መርህ ለመተግበርና የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ ስልጠናው ጉልህ ሚና አንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡ የሥራ ማዕከላትን ለማጠናከር በተጀመሩ ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ወጣቶችን ከአዳዲስ የሥራ ዕድል ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ያነሱት የቢሮ ኃላፊው የማዕከላቱን ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ የሚሰጡ መሰል ስልጠናዎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የሆኑ የሥራ ማዕከላትን እውን ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው የክልሉን ሰፊ የተፈጥሮ ፀጋ በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚኖርባቸውም የቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ብቁ ባለሙያዎች የሚፈልቁባቸው ማዕከላት ለማድረግ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም በአፅንኦት አንስተዋል፡፡
amAM
Scroll to Top