“የኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳሩ በተፈለገው መጠን..
ታህሳስ 8, 2023
“የኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳሩ በተፈለገው መጠን እንዳይሰፋ የሚያግዱ የተዘጉ በሮችን ለማስከፈት የሚመለከታቸውን አካላት ንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡”
ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ‹‹ለኢንተርፕርፕሪነሮች ክፍት ይሁኑ በሮች›› በሚል መሪ ሃሳብ የዓለም አቀፍ የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንትን በተለያዩ ዝግጅቶች ከህዳር 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ እያከከበረ ይገኛል፡፡
የሣምንቱ አካል የሆነው የፓናል ውይይት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንደገለፁት፤ የኢንተርፕሪነርሺፕ ምህዳሩ በተፈለገው መጠን እንዳይሰፋ የሚያግዱ የተዘጉ በሮችን ለማስከፈት የሚመለከታቸውን አካላት ንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡
በቅርቡ እንደሚፀድቅ የሚጠበቀውን የስታርት አኘ አዋጅን ጨምሮ ለፈጠራና ኢኖቬሽን መንግስት እየተሰጠው ያለው ትኩረት ኢትዮጵያን በቀጣዮቹ ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢንተርፕሪነሮች የሚፈሩባት ሀገር ከማድረግ አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሃሰን ሁሴን በሀገራችን የኢንትርፕነርሺፕ ሥነ ምህዳርን ለማስፋት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰው በቀጣይም የፋይናንስ ድጋፍን ፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ፣ የትምህርት ጥራትንና የወጣቶች ክህሎትን በማሳደግ ለኢንተርፕሪነሮች በሮችን ክፍት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
በፈጠራና በኤኖቬሽን ልማት ላይ የተሰማሩና ከግሉ ዘርፍ የተወጣጡ አካላት ተሳታፊ በሆኑበት የፓናል ውይይት በአገራችን የኢንተርፕሪነርሽፕ ልማትን ለማስፋት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚያስችሉ የመፍትሔ አማራጮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሄደዋል፡፡