የአምስት ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና የዲጂታል ክህሎት እንድናጎለብት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል
የአምስት ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና ከዘመኑ ጋር አብረን መራመድ የሚያስችለንን የዲጂታል ክህሎት እንድናጎለብት ምቹ ሁኔታን ፈጥሮልናል ሲሉ በመዲናዋ የኮደርስ ሰልጣኞች ገለጹ።
ወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎታቸውንና እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ መንግስት የአምስት ሚሊየን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብር ዘርግቶ ብዙዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ኢዜአ ስልጠናውን በመውሰድ ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶችንና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማህበርን አነጋግሯል።
ማህበሩ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ወጣቶች የዲጂታል እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ስልጠና እንዲወስዱ እያገዘ እንደሚገኝም አስታውቋል።
ወጣት ደረጄ ማሞ ማህበሩ የአምስት ሚሊየን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የምንወስድበትን ምቹ ሁኔታን ፈጥሮልናል ብሏል፡፡
በማህበሩ እገዛ የዲጂታል ክህሎቱን ለማሳደግ የሚያግዘውን የኮደርስ ስልጠና በመውሰድ ራሱን ለማሻሻል መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም ከኮደርስ መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ የሆነውን ዌብ ፕሮግራሚንግ በመምረጥ ስልጠና እየወሰደ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ ዘገባው የኤዜአ ነው።