Mols.gov.et

የነገው ቀን

መስከረም 10, 2025
የነገው ቀን ኢትዮጵያ በፈጠራና ፍጥነት ዘመኑን ለመዋጀት ጉዞዋን ጀምራለች፡፡ ለዚህ ጉዞ ስኬት የክህሎት ልማት ዘርፉ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህንን የማይተካ ሚናውን በብቃት ለመወጣትም አሁናዊ እና የመጪውን ዘመን ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የስልጠና ስርዓት ተቀርፆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩም የዲጂታል ስነ-ምህዳሩ ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ በዚህም በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ በኢ-ኮሜርስ፣ በትራንስፖርት፣ በግብርና ቴክኖሎጂ እና በታዳሽ ኃይል ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድሎችን መፍጠር ተችሏል፡፡ የማደግ አለኝታ ያላቸውን ዘርፎች በመደገፍ የተገኙ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችንም በእጅጉ ለማላቅ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ለምርትና ምርታማነት እንዲሁም ቀጣይነት ላለው ዕድገት መሰረት ነው። ለዚህም ቴክኖሎጂን መጠቀም የአማራጭ ጉዳይ አይሆንም፡፡ ከዚህ ባሻገር እንደ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች በሙሉ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ ያሉትን አገልግሎቶችን ጨምሮ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ የተካተቱ ተጨማሪ ሥራዎች ከዚህ አንፃር እንደ ማሳያ የሚነሱ ናቸው፡፡ መጪውን ዘመን የሚዋጅ የክህሎት ልማት በማጎልበት፣ ዲጂታል የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን በማስፋት እና ቴክኖሎጂን በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ውስጥ በማካተት ዲጂታል ኢትዮጵያን ለማሳካት ርብርቡ ይቀጥላል፡፡ #የነገውቀን_ዲጂታል_ኢትዮጵያን_እውን_ማድረግ #ዲጂታል_ኢትዮጵያ ጳጉሜን 5 /2017 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
amAM
Scroll to Top