Mols.gov.et

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ልዑካን ቡድን አባላት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላትን ጎበኙ

ነሐሴ 13, 2024
የሳውዲ አረቢያ መንግስት ልዑካን ቡድን አባላት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላትን ጎበኙ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የተመረጡ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ወደ ውጭ አገር ለሥራ የሚሰማሩ ዜጎች አስፈላጊውን ክህሎት እንዲላበሱ የሚያስችሉ ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ማዕከላት መካከል አንዱ የሆነው የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሳውዲ አረቢያ የሥራና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የልዕካን ቡድን አባላት ተጎብኝቷል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ ለሰጠው ትኩረት የተሰማቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን በሥፋት ለሥራ የሚሰማሩባት ዋንኛዋ የመዳረሻ አገር እንደመሆኗ ብቁ ሠራተኞችን ለማፍራት የሚሰጠውን ሥልጠና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተቀራርበው እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡
amAM
Scroll to Top