Mols.gov.et

“የሥራ ፈጠራ ሥነ-ምህዳሩን በማጠናከር ረገድ …

መጋቢት 27, 2026
“የሥራ ፈጠራ ሥነ-ምህዳሩን በማጠናከር ረገድ ስኬታማ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው”፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት በሀገራችን የሥራ ፈጠራ ሥነ-ምህዳሩን (Entrepreneurship Ecosystem) በማጠናከርና ወጣቶች ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ አዳዲስ የንግድ ሐሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ስልታዊ ድጋፎችን እያከናወነ ይገኛል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሰን ሁሴን እንደገለጹት፤ ተቋማወጣቶች የራሳቸውን የፈጠራ ሐሳብ ይዘው ሲመጡ፣ ያ ሐሳብ ወደ ውጤታማ ኢንተርፕራይዝ እንዲያድግ የሚያስችል የክህሎት፣ የማማከርና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት ላይ ነው። ዶክተር ሀሰን አክለውም፣ ከክህሎት ድጋፍ በተጨማሪ የገበያና የፋይናንስ ትስስር ለሥራ ፈጣሪዎች ስኬታማነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም መሠረት ከባንኮችና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ለፈጣሪዎች የብድርና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን የማመቻቸት ሥራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። አሁን ላይ በገበያ ውስጥ የሚታዩ ስኬታማ ስታርታፖች የኢንስቲትዩቱ ስልታዊ ድጋፍ ውጤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ወጣቶች ያላቸውን የፈጠራ አቅም በመጠቀም ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ የኢንተርፕረነርሽፕ ንቅናቄ በሀገራችን ያለውን የሥራ አጥነት ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማፋጠን እንደ ትልቅ መፍትሔ የሚወሰድ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።
amAM
Scroll to Top