የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱን መሰረት በማድረግ እየተከናወነ ያለው የሥራ ዕድል…
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለንን ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡
በውይይታችን የሥራ ስነ-ምህዳሩ ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ምቹ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታን በዝርዝር ተመልክተናል፡፡ በቀጠይ የትብብር ማዕቀፎችን በመለየት በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ሰፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን በቅንጅት ለማከናወን ተግባብተናል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የተጀመሩ ሥራዎችን በማላቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብር ለመሥራት ላሳዩን የላቀ ቁርጠኝነት ከልብ መነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡