የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የምርምርና የማማከር ድጋፍ…
ታህሳስ 6, 2023
” ኢትዮጵያ ማደጓና መበልፀጓ አይቀሬ በመሆኑ የአሠሪና ሠራተኛ አደረጃጀቶች አይቀሬ ለሆነው ነባራዊ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይገባቸዋል፡፡ “
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ2016 የአሠሪና ሠራተኛ ጉባኤ ለተለያዩ አካት እውቅና በመስጠት ተጠነቋል፡፡
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፣ ማህበራዊ ምክክርና የላቀ ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የአሠሪና ሠራተኛ ጉባኤ የጀመርናቸውን የሪፎርም ሥራዎች ሊያጠናክሩ የሚችሉ ግብዓቶች የተገኘበት ነው፡፡
በመድረኩ በየደረጃው የተጀመሩ ሥረዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውንም ለማየት ችለናል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ማደጓና መበልፀጓ አይቀሬ በመሆኑ የአሠሪና ሠራተኛ አደረጃጀቶች አይቀሬ ለሆነው ነባራዊ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በዘርፉ የሚከናወኑ ሥራዎች በሙሉ የዜጎችን ደህንነት፣ ጤንነት እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለሙ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡
ዛሬ እውቅና የተሰጣቸው የአሠሪና ሠራተኛ አደረጃጀቶች የሠራተኛውን ጥቅምና የኢንዱስትሪውን እድገት አጣጥሞ መሄድ እንደሚቻል ያሳዩ መሆናቸውን የጠቆሙት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቀጣይም በብታቸውን አስጠብቀው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በየደረጃው ያሉ አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በመድረኩ ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠር እና ሰላማዊ እንዱስትሪ እንዲሰፍን ከፍተኛ አበርክቶ ለነበራቸው ኢንዱስትሪዎችና የአሠና ሠራተኞች አደረጃጀቶች እውቃና ተሰጥቷቸዋል፡፡