Mols.gov.et

የምንገኝበት ምዕራፍ የእሳቤና የአሰራር ለውጥ ይፈልጋል

ሚያዝያ 19, 2024
የምንገኝበት ምዕራፍ የእሳቤና የአሰራር ለውጥ ይፈልጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚንስትር በዘርፉ የፐብሊክ ኢንተርፕረነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር መገንባት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ለዘርፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እየተሰጠ ነው። በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የዘርፉ አዲስ እሳቤ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ እንደጠቀሱት፣ እስካሁን የመጣንበት መንገድና የለመድናቸው አሰራሮች ወደ ምንፈልገው ከፍታ ስለማያደርሱን አሁን የምንገኝበት ምዕራፍ የእሳቤና የአሰራር ለውጥ ይፈልጋል፡፡ የፐብሊክ ኢንተርፕረነርሺፕና ኢኖቨየሽን ስልጠና ደግሞ የዘርፉ ግቦች ለማሳካት እንደለውጥ መሳሪያ ይወሰዳል ብለዋል። ስልጠናው ፐብሊክ ኢንተርፕሩነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ምህዳር ግንባታ ላይ አተኩሮ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
amAM
Scroll to Top