Mols.gov.et

የምንታወቅበት አፍሪካዊ የሆነ መለያ ያስፈልገናል’። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

ህዳር 22, 2022
የምንታወቅበት አፍሪካዊ የሆነ መለያ ያስፈልገናል’። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር 8ኛው የአፍሪካ አመታዊ የመሀንዲሶች ጉባኤ እና የአፍሪካ መሀንዲሶች ሣምንት ከጥቅምት 28 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንደተናገሩት አፍሪካ የማህበራዊ ሃብት ባለቤት ናት። እነዚህን እሴቶች ታሳቢ በማድረግም የአፍሪካ ሴት መሃንዲሶችን አንተርፕርንሽፕና፣ የአዳዲስ ፈጠራዎች ባለቤት በማደረግ በከተማ ዲዛይን፣ በቤቶች ውበት፣ በሳኒቴሽንና በኮንስትራክሽን /ስማርት ሲት / በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ ማሳያ አላት። ለአብነትም የቴሌኮም እና የትራንስፖርት መሰረት ልማት መስፋፋት ፣ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መታጠቃቸው፣ የአይ ሲቲ ፓርኮች መገንባታቸው እንዲሁም በቅርቡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የብየዳ ክህሎት ስልጠና የምትሰጥ ብቸኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሆናለች ፡፡ በቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት፣ የብየዳ ስልጠና ማዕከል ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የብየዳ ኢንስቲትዩት ብቁ የብየዳ ስልጠና ማዕከልነት የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት አግኝተናል፤ ስለዚህ በሌሎች አፍሪካ ሃገራትም በተመሳሳይ የተለያዩ የአዳዲስ ፈጠራና አንተርፕርንርሽፕ ሥራዎች በመኖራቸው አፍሪካን ተመራጭና በቀጣይ ተስፋ ያላት አህጉር ለመሆኗ ማሳያ ነው በልዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የአፍሪካ ሴት መሃንዲሶች የየአገራቱን ጉልህ ችግር በአንክሮ ስለሚረዱ የሥርዓተ-ፆታ አለመመጣጠንን፣ በቴክኖሎጂ የበለጸገ ከተማ አንዲሁም ፈጣንና ቀላል የሆኑ መጓጓዣዎች፣ የቤትና የመሰረተ ልማት ግንባዎች ላይ ሴቶችን ከማሳተፍ ባለፈ ወደፊት ማምጣትና በአፍሪካዊያን ብቻ የተሰራ የምንታወቅበት አፍሪካዊ የሆነ ብራንድ መለያ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡
amAM
Scroll to Top