Mols.gov.et

የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ተገመገመ

ህዳር 29, 2024
የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ተገመገመ የተጠሪ ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ተገምግሟል። በመድረኩ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲቲዩት፣ የቱሪዝም ኢንስቲቲዩት እና የኢንተርፕርነር ልማት ኢንስቲትዩት እንዲሁም የአምስቱ የግብርና ኮሌጆች ዕቅድ አፈፃፀም በየተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋማቱ የተሻለ አፈፃፀሞችን አልቆ ማፅናት እና ክፍተቶችን በፍጥነት ማረምና መሙላት እንደሚገባ አሳስበው ይህንንም በልዩ ዕቅድ ለመመለስና ሪፎርሙን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል::
amAM
Scroll to Top