Mols.gov.et

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ስርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አገኘ

መስከረም 9, 2024
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ስርዓት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አገኘ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የሚሰጡት ስልጠና ለሥራ ገበያው ምላሽ የሚሰጥ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብቃት ምስክር ወረቀት የርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት ምልዕት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትና አግባብነትን ለማሻሻል መሰረተ ሰፊ የሪፎር ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 20 ተቋማትን ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን እንዲያሟሉ በተያዘው ዕቅድ እስካሁን የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት ችለዋል፡፡ የሀዋሳ ፖሊቴክኒከ ኮሌጅ ሌላኛው የአይሶ ሰርተፊኬት ያገኘና በሀገራችን የISO 21001:2018 ሰርተፍኬት ያገኘ የመጀመሪያው ተቋም ነው ብለዋል፡፡ የሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የISO 21001:2018 ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ባለቤት መሆኑ የጥራት ሥራ አመራርን ከመተግበር አንፃር እንደ ሀገር ያለበትን ደረጃና እየተሰራ ያለውን ውጤታማ ሥራ የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም ሁሉም የቴክኒክና ተቋማት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የሥልጠና እና የአስተዳደር ስርዓትን እያሟሉ በዚህ ስርዓት እንዲመዘገቡ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሲዳማ ክልል የሥራ ፣ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው ኮሌጁ ከዚህ በፊት ከነበሩበት በርካታ ችግሮች በመውጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለውን ሰርቴፊኬት ማግኘቱ በዘርፉ የተገኘ ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል ።
amAM
Scroll to Top