Mols.gov.et

ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት

ህዳር 20, 2025
ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተከብሯል፡፡ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ በአቶ አብዱሠላም ሸንገል የኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንት የሚከበርበት ዋና ዓላማ ሥራ ፈጣሪ ትውልድን ለመፍጠር የሚያስችል ግንዛቤን በሥፋት ለማሰጨበጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የሥራ የዝግጁነት መጓደል በስፋት የሚስተዋል ችግር መሆኑን የገለፁት የቢሮ ኃላፊው ‹‹የኢንተርፕረነርሺፕ እሳቤን በመላበስ ራሳችንና አካባቢያችንን መለወጥ ይጠበቅብናል›› የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመድረኩም በኢንተርፕረነርሺፕና ሥራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ገለፃ ቀርቦ ውይይት እንደተካሄደበት ከክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል፡፡
amAM
Scroll to Top