Mols.gov.et

ክልሉ አሸናፊ ለሆኑ ሴት ስራ ፈጣሪዎች…

ጥር 1, 2026
ክልሉ አሸናፊ ለሆኑ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የ1.8 ሚሊዮን ብር ሽልማት አበረከተ የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ በሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞችን በማወዳደር የገንዘብ ድጋፍ አበርክቶላቸዋል፡፡ የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሴት ወጣቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በብዙ ሴቶች አይደፈሩም ሲባሉ በቆዩ የሙያ ዘርፎች በማሰልጠን የሥራ ባለቤት እንዲሆኑና በክህሎታቸውና በንግዳቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አደርጓል ብለዋል፡፡ በሴቶች ባለቤትነት የሚመሩ የ19 ኢንተርፕራይዞችን የቢዝነስ ሀሳብ በማወዳደር አሸናፊ ለሆኑ ዘጠኝ ኢንተርፕራይዞች 1.8 ሚሊዮን ብር በሽልማት እንዳበረከተላቸውም ተጠቁሟል፡፡ የማህበረሰብ ምሰሶ ተብለው የሚጠቀሱት ሴቶች በሥራ ሥምሪት ሲሳተፉ የሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡ በተለይ በግብርና፣ በንግድ እና በአገልግሎት በመሳሰሉ ዘርፎች ትልቅ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ በተጨማሪም ሴቶች የሚያገኙት ገቢ 90 በመቶ ለቤተሰብ፣ ለልጆች፣ ለትምህርት እና ለቤተሰብ ምግብ ዋስትና እንሚያውሉትም እንዲሁ፡፡ ይህ ተጨባጭ ሁኔታ “ሴቶችን ማብቃት ማህበረሰብን ማብቃት ነው” የሚለውን መርህ ያጠናክራል፡፡
amAM
Scroll to Top