Mols.gov.et

በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ክቡር ጁንግ ካንግ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ…

መጋቢት 11, 2025
በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ክቡር ጁንግ ካንግ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በዚህም ልህቀት ማምጣት በሚያስችሉ የክህሎት ልማት እንዲሁም የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ተግባብተናል፡፡ ኮሪያ በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለኢትዮጵያ ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል እንዷ ስትሆን ትብብሩ ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ የሚያሳድገው ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያና ኮሪያ ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ክቡር አምባሳደር ጁንግ ካንግ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ግንኙነቱን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ! የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
amAM
Scroll to Top