Mols.gov.et

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አመራርና ሰራተኞች ጋር የዘጠኝ ወራት የመንግስት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውጤታማ ውይይት

ሚያዝያ 22, 2025
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አመራርና ሰራተኞች ጋር የዘጠኝ ወራት የመንግስት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ መድረኩ የተከበሩ ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን የሀገር አቀፉን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀምን ከዓለም አቀፉ ሁኔታ፣ ከማክሮ ኢኮኖሚ እና ከሪፎርም አፈፃፀምና አዝማሚያዎች ጋር በማስተሳሰር በዘላቂ ልማታችን ላይ ያለውን አንድምታ አይነተናል፡፡ ከዚህ ባሻገር የመሠረተ ልማት እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን ጨምሮ ማህበራዊ አካታችነት እና ሁለተናዊ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የተሠሩ ሥራዎችን እና የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር ተመልክተናል፡፡ በተደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብም ተስፋ ሰጪና ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በቀሪ ወራት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነትና የተቋም ግንባታ ጉዳዬች ላይ በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ለማላቅ በትጋት ፍጥነትና ፈጠራን ማዕከል ያደረገ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባን ተግባብተናል፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በመገኘት ውይይቱን ስለመሩልንና ለቀጣይ ሥራዎቻችን መነሳሳትን የሚፈጥር ግብዓት ስለሰጡን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ! የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
amAM
Scroll to Top