እንኳን ደስ አለን!
እንሆ! የህዳሴው ግድባችን ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፡፡ የኩስመና ታሪካችንም ተዘጋ። የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞም ጀመረ።
ከጉባ ሰማይ ስር የተንጣለለው የንጋት ሀይቅ የአይቻልም መንፈስን የሰበረና የኢትዮጵያውያንን ጥንካሬና የመቻል አቅም ህያው ማሳያ ነው። ይህ ስኬት የሁላችን የጋራ ድል ነው።
ህዳሴ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ግድብ ብቻ አይደለም። የላባችንና የደማችን፣ የጥረታችን፣ የአንድነታችን እና የጋራ ህልማችን መገለጫ እንጂ። ለዘመናት “እንችላለን?” ለሚለው የትውልዶች ጥያቄ በፅኑ “አዎ! እንችላለን!” ብሎ የመለሰ ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው። የህዳሴ ግድብ የትውልዱ ዳግማዊ አድዋ ነው።
እንኳን ደስ አለን!