Mols.gov.et

ተስፋ ሰጪው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት …

ታህሳስ 24, 2024
ተስፋ ሰጪው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት … የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተሰጠው ተልዕኮ አንዱና ዋነኛው የማክሮ ኢኮኖሚው ትልቁ ፈተና የሆነውን የሥራ አጥነት ምጣኔን በዘላቂነት መቀነስ ነው፡፡ በዚህም ፈጠራና ፍጥነት የታከለባቸው ሥራዎችን በየደረጃው ተግባረዊ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ተጨባጭና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም መታየት ጀምረዋል፡፡ ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት መርሃ ግብር ተጠቃሽ ነው፡፡ በዘርፉ የአምስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ የኦሮሚያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው በሰጠው ትኩረትና ተግባዊ እየተደረገ ባለው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት ፕሮግራም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቶበታል፡፡ በክላስተር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘው በዚህ ፕሮግራም ከ3ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ከመቶ ሺህ በላይ ወጣቶችንም የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም አመላክተዋል፡፡ በክልሉ እየተተገበረ የሚገኘው የወጣቶች የተቀናጀ ልማት ሥራ በስንዴ ልማት፣ በጎጆ ኢንዱስተሪ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በቅመማ ቅመም፣ በአሳ እርባታ፣ በከብት ማድለብና መሰል ክላስተሮች ተለይተው እንደሆነ ያመላከቱት ምክትል ኃላፊው የክልሉ መንግስት የተለያዩ መንግስታዊ ድጋፎች እያደረገ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
amAM
Scroll to Top