Mols.gov.et

በክልሉ በ8 ወራት ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ቢሮው አስታወቀ

መጋቢት 11, 2026
በክልሉ በ8 ወራት ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ቢሮው አስታወቀ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ባለፉት ስምንት ወራት ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል። ይህ አፈጻጸም ክልሉ ካስቀመጠው ግብ አንጻር ከፍተኛ ውጤት የታየበት መሆኑም ነው ቢሮው ያስታወቀው። የቢሮው የሥራ ስምሪት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አለነ እንደገለጹት፣ ይህ ስኬት የተመዘገበው ቢሮው ተግባራዊ እያደረገ ባለው “አዲሱ የክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ” እሳቤ ነው። ስራው በዘልማድ ከመመራት ወጥቶ በዕውቀትና በክህሎት ላይ እንዲመሠረት መደረጉ ለውጤቱ መገኘት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል። የተፈጠሩት የሥራ ዕድሎች ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ያካተቱና ፍትሃዊነትን የተከተሉ መሆናቸውንና በቴክኒክ ኮሚቴው መካከል ያለው የተቀናጀ አሠራር ለሥራው መፋጠን ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱም ነው የተገለፀው፡፡ የተመዘገበው ውጤት ዘላቂ እንዲሆን የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ መዘመን እንዳለበት የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴው በክልሉ የሚታየውን ሥራ አጥነት ለመቀነስ ፋይዳው የላቀ መሆኑ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
amAM
Scroll to Top