Mols.gov.et

በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ …

የካቲት 24, 2026
በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጨባጭ፣ ተስፋ ሰጪና አዳጊ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ያለውን ውዝፍ፣ አሁናዊ እና የመጪውን ጊዜ ሀገራዊ ፍላጎት መመለስ በዘርፉ ተግባራዊ የተደረገው ፎርም ዋና ማጠንጠኛ ነው። በዚህ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተቀርፆ ወደ ሥራ እንዲገባ የተደረገው “ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ” ስትራቴጂ፣ ዛሬ ላይ በሥራ ዕድል ፈጠራ ስነምዳር ውስጥ ተጨባጭ፣ ተስፋ ሰጪና አዳጊ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል። በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ፣ ከ2.6 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል። የሥራ ዕድል ፈጠራውን በዘርፍ ስንመለከተው፤ የአገልግሎት ዘርፉ የ40.5 በመቶ ድርሻ በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲመራ፣ የግብርናው ዘርፍ 37.5 በመቶ እና ቀሪው 22 በመቶ የሚሆነው የሥራ ዕድል በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተፈጠረ ነው። ከተፈጠረው አጠቃላይ የሥራ ዕድል ውስጥም 53 በመቶው በከተማ አካባቢዎች ሲሆን፣ ቀሪው 47 በመቶው ደግሞ በገጠር ለሚኖሩ ዜጎች የተመቻቸ ነው። ይህ ስርጭት በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ ሥራ ፈላጊዎችን ተደራሽ ለማድረግ በመንግስት የተሰጠውን ልዩ ትኩረት ማሳያ ነው። የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በፈጠራና በፍትነት በማከናወን ከዕድገት ተኮር ዘርፎች ጋር ለማስተሳሰር በየደረጃው የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረትና ርብርብ፣ ለዚህ ታላቅ ውጤት መገኘት የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል። ለዜጎች ሰፋፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በማሳደግና የኢንተርፕሪነርሺፕ ምህዳሩን በማስፋት፣ ዜጎች የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚደረገው ድጋፍ፤ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለሀገራዊው የድህነት ቅነሳ ጉዞ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው።
amAM
Scroll to Top