Mols.gov.et

በከተማው ልማት ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘ ተቋም

መስከረም 23, 2024
በከተማው ልማት ላይ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘ ተቋም የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በከተማው ክህሎት መር አጫጭር እና መደበኛ ሥልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ ተቋም ነው። ተቋሙ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት ዘርፍ ላይ ያደረገውን የሪፎርም ትግበራ ተከትሎ በአይሲቲ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ በእንጨት፣ በቆዳና እና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተጋ ይገኛል፡፡ ኮሌጁ ከሥልጠና በላይ ባለው ተልዕኮ የሥልጠና ጥራቱን የሚያረጋግጡና የውስጥ ገቢ አቅሙን የሚያሳድጉ ተግባራት እያከናወነ ነው፡፡ በዚህም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተኪ ምርቶችን እያመረተ ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት ደረጃቸውን የጠበቁ የፈርኒቸር ውጤቶችን እያቀረበ ይገኛል፡፡ የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ለሚገኘው የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ዘመናዊ የቆሻሻ መጣያዎች እና ተንቀሳቃሽ የፈጣን ምግብ ማዘጋጃና መሸጫ ሱቆችን እያመረተ በማቅረብ በከተማው ልማት ላይ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ይህም የኮሌጁ ሰልጣኞች የቴክኖሎጂ ሽግግርን ዕውን ለማድረግ ተጨማሪ አቅም እና የሥራ ባህል እንዲኖራቸው አስችሏል፡፡ በተመሳሳይ ኮሌጁ ከከተማ ውበትና እና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት እና ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማው በኮሪደር ልማት አረንጓዴ ሥራዎች ላይ ለሚሳተፉ ዜጎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን ኮሌጁ ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡
amAM
Scroll to Top