በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቬርስቲቼል ጋር የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራን የተመለከቱ የድጋፍ አግባብ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል።
በውይይታችን የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን እና እያስገኙ ያለውን ተጨባጭ ውጤቶችን ተመልክተናል።
የክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነትን ጨምሮ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮችንም በዝርዝር አይተናል።
በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቬርስቲቼል የሁለቱን ሀገራት የረዥም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ለማጠናከር ላሳዩን ተነሳሽነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!