Mols.gov.et

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ካምፓስ የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ አገኘ

ሚያዝያ 25, 2025
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ካምፓስ የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ አገኘ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን ለኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ካምፓስ ሰጥቷል፡፡ ኮሌጁ ሰርተፊኬቱ የተሰጠው ለጥራት የሥራ አመራር ሥርዓት የተቀመጡ ዓለም አቀፍ መመዘኛ መስፈርቶችን ማሟላቱን በተደረገ ኦዲት ተረጋግጦ ነው፡፡ ይህም ብየዳን ጨምሮ የተለያዩ የሙያ መስኮች ላይ የሚሰጠው ስልጠና፣ የሚያከናውናቸው የቴክኖሎጂና የምርምር እንዲሁም የሥልጠና መሳሪያዎች የጥገና ሥራ እና የማህበረሰብ አገልግሎትና የድጋፉ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የሚያሟላ ተቋም እንደሆነ እውቅና የሚሰጥ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘርፉ ያሉት ተቋማት ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ያሟሉና የሚሰጡት ስልጠና፣ ሰርተፊኬትና አገልግሎት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ማድረግ የሪፎርሙ አካል አድርጎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ እንደየ ተቋማቱ ባህሪ የISO 17024:2012፣ ISO 9001:2015 እና ISO 21001: 2018 የጥራት የሥራ አመራር ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡ በዚህም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጀምሮ በተዋረድ ያለው አደረጃጀቱ የጥራት አመራር ስርአትን በመተግበር ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማቱና የሙያ ምዘና ማዕከላቱ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው እንዲሆኑ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም በሁለተኛው ምዕራፍ የሁሉንም ክልል የሙያ ምዘና ማዕከላቱን ጨምሮ 70 የሚሆኑ የዘርፉ የሥልጠና ተቋማት የጥራት አመራር ስርዓትን እንዲያሟሉ በትኩረት እየተሰራ ሲሆን በእስካሁኑ ሂደትም የተቋለያዩ የስልጠና ተቋሞቻችን የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ አግኝተዋል፡፡
amAM
Scroll to Top