Mols.gov.et

በሀረሪ ክልል ሀገር በቀል እውቀቶችን …

ጥር 4, 2026
በሀረሪ ክልል ሀገር በቀል እውቀቶችን በማጎልበት ሙያዊ በሆነ የምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ቅድመ ዝግጅት ስራ ተጀመረ የሀረሪ ክልል የልህቀት ማእከልና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሀገር በቀል ሙያዎችን ለማሳደግና በምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ለማስቻል የቅድመ ዝግጅት ሥራ አስጀምረዋል፡፡ የክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ ሀገር በቀል እውቀቶችን በማሳደግ በሀገር ብልፅግና ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሀገር በቀል እውቀቶችን በማጎልበት ሙያዊ በሆነ ምዘና ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ ሙያተኞች ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል። በክልሉም የኢናይ አቢዳ ማሰልጠኛ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የሙያዎቹን ምዘናና ደረጃ (level) የማውጣት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ የሀረሪ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ሃላፊ አቶ በዳሳ ገመዳ፤ ሀገር በቀል የሙያ ደረጃዎችን በተከተለ መልኩ እየተሰጡ የሚገኙ ስልጠናዎችን በማጠናከር ወደ ኢንዱስትሪው እንዲገቡ የማስቻል ስራዎች በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በመርሃግብሩ ላይም የሀረሪ ክልል ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለሞያዎችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል።
amAM
Scroll to Top