Mols.gov.et

ስምምነቱ በግብርና ልማት ዘርፉ የተሰማሩና ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንተርፕራይዞችን የፋይናነስ አቅርቦት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

መስከረም 2, 2024
ስምምነቱ በግብርና ልማት ዘርፉ የተሰማሩና ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እንተርፕራይዞችን የፋይናነስ አቅርቦት ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች ፋይናንስ ማቅረብ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ የተፈራረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ አያሌው(ዶ/ር) ናቸው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ስነ-ስርዓት ወቅት እንደገለጹት፤ ግብርና በዘመናዊ መንገድ ለመስራት እየተደረገ ባለው ጥረት የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅሙ ማደጉን ገልጸው ይህ ስምምነትም በግብርና ልማት ዘርፍ የተሰማሩ እና ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ ችግር መቅረፍ ላይ ትኩረቱ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለስራ ፈጣሪዎች ምቹ ምህዳር ለመፍጠር እያደረገ የሚገኘውን ጥረት አድንቀው በግብርናው ዘርፍ የወጣቶችን አቅም ለመጠቀምና፣ እራስን ለመቻል እና አለፍ ሲልም ኤክስፖርት ለማድረግ እየተደረገ የሚገኘውን ጥረት የፋይናነስ አቅርቦቱ በእጅጉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው ባንኩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የሚያቀርበው ይህ የፋይናንስ አቅርቦት የወጣቶች ኢንቨስትመንት ለማበረታታት እና በግብርና ሥራ ፈጠራ የተሰማሪ ኢንተርፕራይዞች የአዕምሮ ውጤታቸውን ያለምንም የፋይናንስ ተግዳሮት ወደ መሬት ማውረድ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡ የፋይናንስ አቅርቦቱ ከተያዘው በጀት አመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን ለአጠቃላይ ስራው 43 ሚሊዮን ዶላር ተመድቧል።
amAM
Scroll to Top