ዘመን ተሻጋሪ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ለማድረግ እንተጋለን -ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 30/2017(ኢዜአ)፡-ዘመን ተሻጋሪ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ለማድረግ እንተጋለን ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ማሻሻያ የዝግጅት ምዕራፍን በላቀ ደረጃ በማጠናቀቁ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዕውቅና ተሰጥቶታል።
በዕውቅና መርሃ-ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል፥ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ተወዳዳሪና ውጤታማ የምትሆነው ዘላቂና አስተማማኝ ተቋማትን ስትገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ ተቋማቸው የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የሪፎርም ተግባር ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል።
ሚኒስቴሩ የፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍን በአግባቡ በመወጣት ለትግበራው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በዚህም ዘመን ተሻጋሪ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ለማድረግ እንደሚተጉም ገልጸዋል።