Mols.gov.et

መድረኩ በተቋሙ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ዕይታ ይበልጥ ማጎልበት የሚያስችል ነው፡፡

ነሐሴ 15, 2024
መድረኩ በተቋሙ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ዕይታ ይበልጥ ማጎልበት የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በየወሩ ጠዋት ከ1፡00 እስከ 3፡00 በአዳዲስ አሰራሮች(innovation) ላይ አተኩሮ የሚያካሄደው መድረክ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ በSystem Thinking እና የሥልጠና እና የገበያ ፍላጎት አለመጣጣም ላይ ያተኮረ መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተናጠል ሩጫ እና አስተሳሰብን አስወግዶ ቅንጅታዊ እና አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደረገ ተቋም መሆኑን ገልጸው በየወሩ የሚካሄደው የማለዳ ውይይትም ይህን ያዳብረዋል ብለዋል፡፡ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች በተለመደው መንገድ በመሄድ አይፈታም ያሉት ክብርት ሚኒስትር ያደሩ ተግባራት፣ የአሁንና የቀጣይ ፍላጎቶችን ያስተሳሰረ ችግር ፈቺ ዕይታና አካሄድ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል፡፡ ነባሩን የአስተሳሰብ፣ የባህል እና የሲስተም ችግር በአንድ ጀንበር የሚፈታ ባይሆንም ስራው እያደገ መሄዱን ማረጋገጥና ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ የአመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማቱ አመራርና ሠራተኞች የሚያደርጉት ወርሃዊ የማለዳ ውይይት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና ሰላማዊ ኢንዱሰትሪ ግንኙነት ላይ የሚስተዋሉ ሀገራዊ ችግሮችን ፈጠራ በታከለበት አግባብ ለመፍታት ያለመ ነው።
amAM
Scroll to Top