Mols.gov.et

ለወጣቶችና ሴቶች አዲስ የሥራ ዕድል የከፈተው …

ሚያዝያ 21, 2026
ለወጣቶችና ሴቶች አዲስ የሥራ ዕድል የከፈተው የግብርና ኢንተርፕራይዞች ልማት ፕሮጀክት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የግብርና ኢንተርፕራይዞችን ለማዘመንና የእሴት ሰንሰለቱን የተከተለ የሥራ ዕድል ለወጣቶችና ሴቶች ለመፍጠር ያለመ ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከክልል ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በፕሮጀክቱ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው በዙም (Zoom) ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ ግብርናውን ከባህላዊ አሰራር በማውጣት ወደ ዘመናዊ የንግድ ሥራ (Agri-Business) ለመቀየር አቅም ሰንቆ የተነሳ ነው። ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚዘልቅና ዘንድሮ ወደ ትግበራ የገባ መሆኑን ገልጸው አፈጻጸሙን ውጤታማ ለማድረግና የታለመለትን ግብ እንዲመታ ክልሎች ፕሮጀክቱን በልዩ ትኩረት የቅርብ ክትትል በማድረግ እንዲደግፉ አሳስበዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በግብርና ዘርፍ የወጣቶችንና የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ዘላቂ ምህዳር መፍጠሪያ በመሆኑም በባለቤትነት ስሜት አፈጻጸሙን መከታተል እንደሚገባ ጨምረው ገልጸዋል እያንዳንዱ አካባቢ ያለውን የግብርና ምርት አቅም መለየት ለሥራ ዕድል ፈጠራው ስኬት መሠረት ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ይህም በየአካባቢው ያለውን ጸጋ መሠረት ያደረገ እሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡ በግብርና ኢንተርፕራይዝ የሚሳተፉ ዜጎች የሳይኮሜትሪክ ፈተና (Psychometric Test) እንዲወስዱ በማድረግ ብቃታቸውን መሰረት ያደረገ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ የዘርፉ ተቋማትን የማስጸም አቅም የሚገነባ ሲሆን ለኢንተርፕራይዞች ደግሞ ቴክኒካዊ ስልጠናዎች፤ የንግድ ልማት ምክር አገልግሎት፤ የፋይናንስ አቅርቦት እና የተሳለጠ የገበያ ትስስር ድጋፍ ያደርጋል።
amAM
Scroll to Top