ኢኮኖሚያዋና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል:: ክብርት አለሚቱ ኡመድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር
ታህሳስ 4, 2024
ኢኮኖሚያዋና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል::
ክብርት አለሚቱ ኡመድ
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጋምቤላ ክልል ጋር በመተባበር ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳር ግንባታ ላይ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ- መስተዳድር ክብርት አለሚቱ ኡሞድ በመድረኩ ላይ ባስተላለፊት መልዕክት፤ መንግስት የሥራ ዕድል ፈጠራውን ለማበረታታት በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።
በዚህም ተጨባጭ ውጤት እየታየ ቢሆንም ከሚፈለገው አንፃር ግን በዘርፉ ብዙ እንድንሰራ ይተበቃል።
ኢኮኖሚያዋና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል::
ስለሆነም በመስኩ የሚታየውን ውስንነት ለመሻገር አመራሩ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፣ በክልሉ የተጀመረው የሰላም ግንባታ ሂደት ዘላቂ እንዲሆን ጠንካራ በሆነ የልማት ሥራዎች መታገዝ ይኖርበታል።
የሚሰጠው የፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳር ግንባታ ስልጠና ክልሉ ያለውን የልማት ፀጋ በሙሉ አሟጦ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም የአመራሩ ሚና እና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር ሁሉም ይህንን በመገንዘብ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡