በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የአፍሪካ ብየዳ ፌዴሬሽን መደበኛ ዓመታዊ ጉባዔ እና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በብየዳ ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ጉባኤ በብየዳ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ ምክክር፣ የልምድ ልውውጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የብየዳ ክህሎት ውድድር እና የመስክ ጉብኝት ይደረጋል ፡፡
ብየዳ ልህቀት ማዕከል እየተካሄደ ባለው ውድድር 5 ሴት የብየዳ ባለሙያዎችን ጨምሮ 23 ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ውድድሩን ኢትዮጵያውያን እና ናይጄሪያውያን ዳኞች እየመሩት ይገኛል።