የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው
ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የዜጎችን ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማሳደግ ተቋማዊ የመፈጸም አቅም ማጠናከር፣ የአሠራር ጥራትን ማሻሻልና የአፈጻጸም ክፍተቶችን መፍታት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ።
ክብርት ሰላማዊት ይህን የገለጹት ከአሠሪና ሠራተኛ ጉዳዮች ዘርፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚዎችና ዴስክ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተወያዩበት መድረክ ላይ ነው።
በውይይቱ በዘርፉ እስካሁን የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች ቀርበዋል፡፡
ክብርት ሰላማዊት፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ የመንግሥት ዋና ትኩረት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህን ግብ ለማሳካት ተቋሚ የመፈጸም አቅምና የአሠራር ጥራት ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዘርፉ ያሉ ጥንካሬዎችን በመለየት ጥሩ አፈጻጸሞችን ማጠናከርና ማስቀጠል፣ እንዲሁም ያሉ ክፍተቶችንና ማነቆዎችን ከመሠረታቸው በመፍታት ውጤታማና ዘላቂ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።