Mols.gov.et

የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ጥምረት… ለላቀ ስኬት !

January 2, 2024
የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ጥምረት… ለላቀ ስኬት ! የውጭ ሃገር የሰራተኛ ስምሪት የዜጎቻችንን መብት፣ ደህንነትና ጥቅም በማስጠበቅ የሃገራችንን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የተጀመሩ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የወሩን አፈጻጸም ገምግመናል። በዘርፉ የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጥን ሃገራችን በሰራተኛ ስምሪት ባለፉት አምስት ወራት ከ144,825 በላይ ዜጎችን ለስራ ወደ ውጪ ማሰማራት መቻሉ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑን እንዲሁም ለበርካታ ዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል አቅም መገንባቱን ተመልክተናል። በዚህም የተጀመሩ ስራዎች በጥሩ ደረጃ ላይ መሆናቸውን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የተጀመረውን ጠንካራ የቅንጅት ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል። ክቡር አምባሳደር ግርማ ለሥራው ውጤታማነት እያደረጉት ላሉት የቅርብ ክትትል እንዲሁም ርብርብ እያደረጉ ላሉ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
Scroll to Top