Mols.gov.et

ከ218 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የማዕክ-ዱግሲየ የክህሎትና የእደ-ጥበብ ኮሌጅ

June 11, 2026
ከ218 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የማዕክ-ዱግሲየ የክህሎትና የእደ-ጥበብ ኮሌጅ ተመረቀ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ,በአውባሬ ከተማ ከ218 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የማዕክ-ዱግሲየ የክህሎትና የእደ-ጥበብ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል። ሪቫን በመቁረጥ ኮሌጁን በይፋ ያስመረቁት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር እና የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ጋይድ ናቸው። ይህ ግዙፍ የክህሎት ማሰልጠኛ ተቋም በ(25ሺ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፥ በውስጡም 21 የተለያዩ የሕንጻ ብሎኮችን አካቷል። ኮሌጁ በተለያዩ የሙያና የቴክኒክ ዘርፎች በየዓመቱ ለ1,500 ሰልጣኞች ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለው ተገልጿል። ተቋሙ የተሟላ የትምህርትና የማሰልጠኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ እንደ የተማሪዎች መኝታና የመመገቢያ አዳራሾች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተግባር ልምምድ ማድረጊያ ማዕከላት (ወርክሾፖች)፣ የአስተዳደር ቢሮዎችና አጠቃላይ አገልግሎት መስጫዎችን በውስጡ ይዟል። ከዚህ በተጨማሪም የዚህ መሰል ከፍተኛ ኮሌጆችን ደረጃ የጠበቁ የተማሪዎች መዝናኛ ስፍራዎችና የስፖርት ማጫወቻ ሜዳዎች ተካተውለታል። በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ማጠቃለያ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አከናውነዋል።
en_USEN
Scroll to Top