Mols.gov.et

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች…

June 25, 2024
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማት የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች የደረሱበትን ደረጃ የሚገመግም የውይይት መድረክ ተካሄደ ። የሪፎርም ቡድኑ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ባካሄዱት ውይይት በሚኒስቴር መ/ቤቱና በተጠሪ ተቋማት ከአሰራርና አደረጃጀት አንፃር ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ነባራዊ ትንተና መሰራቱ ተገልጿል ። በሥራ ላይ ያሉና መሻሻል የሚገባቸው ፖሊሲዎችን ፣ አዋጆችን ደንብና መመሪያዎችን የመለየት ሥራ መሰራቱም በመድረኩ ተጠቁሟል ። ምቹ የሥራ ሁኔታን ከመፍጠር አንፃር የህፃናት ማቆያ ፣ የካፍቴሪያ፣የሸማቾች ህብረት ሥራና መሰል አገልግሎቶችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም በመድረኩ ተመልክቷል ። አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የማድረግ ሥራ ከሁሉም ቅድሚያ እንደተሰጠው የተገለፀ ሲሆን የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የISO 9001፡ 2015 የጥራት ደረጃን የመተግበር ሒደት በሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተብራርቷል ።
en_USEN
Scroll to Top