Mols.gov.et

mols admin

News

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የመፃኢ ጊዜ እድላችንን ከሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የመፃኢ ጊዜ እድላችንን ከሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ ከመላው ሀገሪቱ ለተወጣጡ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ አሁን ያለንበት ጊዜ እውቀት ብቻውን ምሉዕ እንደማያደርግ ከግምት በማስገባት ዓለም ላይ ለክህሎት ልማት ልዩ ትኩረት የተሰጠበት ወቅት ነው፡፡
እኛም እንደ ሀገር በዘርፉ መሰረት ለመጣል ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በቅርቡ ለሀገራዊ ፍላጎቶቻችን ምላሽ የሚሰጥ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ይህም በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ላይ ይስተዋል ነበረውን ክፍተት የሚሞላ ብቻ ሳይሆን የሥልጠና ስርዓታችን ጊዜውን የዋጀና ለሀገራዊ ልማትና ብልጽግና ጉዞ የበኩሉን ድርሻ መወጣት የሚችሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያስችላል፡፡
ፖሊሲውን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተግባራዊ ያደረገው አዲሱ የዘርፉ እሳቤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ ልማት ፍላጎት የሚመልስ፣ በዘርፉ የነበሩ አለመጣጣሞችን የሚፈታ እንዲሁም አሰልጣኞችም ሆኑ ሠልጣኞች ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ይህም የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ እንደ ሀገር የመፃኢ ጊዜ እድላችንን ከሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አሁን የሚሰጠው ስልጠና በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ አሰልጣኞች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ባህሪያዊና ቴክኒካዊ ብቃቶችን በማሳደግ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት በ17 የስልጠና ማዕከላት የሚሰጠው ስልጠና በዘርፉ ልህቀትን ለማምጣት የሚያስችል እንደሆነ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ 24 ሺህ የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ጠቁመዋል፡፡

Read More »
News

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት”

“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት”
“ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ የአሰልጣኝ መምህራኖች ስልጠና ተጀመረ፡፡
በዘርፉ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የአሰልጣኞችን ግንዛቤ ከማሳደግ ባለፈ ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት ማዘጋጀት ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
በዚም 17 የስልጠና ማዕከላት 24 ሺህ የሚጠጉ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ
ነሃሴ 22/2016
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Read More »
News

24 ሺህ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነገ ይጀመራል፡- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

24 ሺህ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነገ ይጀመራል፡- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
******************
ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ 24 ሺህ ገደማ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡
የዘመኑ የሥራ ገበያው የሚፈልገውን እውቀትና ክህሎት የተላበሱ ባለሙያዎችን ከማፍራት አኳያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ሚንስትሯ ገልፀዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ያሉት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፤ የሥልጠና ጥራትንና አግባብነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ዘርፉ ለሀገራዊ የብልጽግ ጉዞ የሚጫወተውን ሚና ለማላቅ ያለመ መሰረት ሰፊ ሪፎርም ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡
“በዘርፉ ያሉን አሰልጣኝ መምህራን የኢንዱስትሪው አማካሪ፣ አስተባባሪ እና ባለሙያም ጭምር በመሆናቸው በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት ከመሙላት ባሻገር የየአካባቢውን ችግር ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ረገድ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው” ብለዋል፡፡
የአሰልጣኞች መድረክ ዓላማ ግንዛቤን ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት እንዲዘጋጁ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
ከነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው መድረክ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ አሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃትና በትጋት እንዲከታተሉ የስራና ክህሎት ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትብብር …

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትብብር በፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳርን ምቹ ለማድረግ ያለመ ስልጠና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች መሰጠት ጀምሯል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ- መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰውና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Read More »
News

በጀርመኗ ላይፕዚግ የደመቀው የእንጦጦዋ ፍሬ …

በጀርመኗ ላይፕዚግ የደመቀው የእንጦጦዋ ፍሬ …
አዲስ አበባ በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ አደባባይ እንደተሰየመላትና በሁለቱ የእህትማማች ከተሞች አጋርነት 20ኛ ዓመት የማክበር ስነ-ስርዓት ላይ ተመርቆ ስለመከፈቱ ተዘግቧል፡፡
በታሪካዊቷ የላይፕዚግ ከተማ ይህ አደባባይ መሰየሙ በሁለቱ ከተሞች ብቻ ሳሆን በሀገራቱ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር ነው፡፡
ለመሆኑ የሁለቱ የእህትማማች ከተሞች መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር እንደሆነ የተነገረለት ይህ አደባባይ ላይ የቆመው ሀውልት የተቀረፀው በማን ነው? የሚል ጥያቄ አንስተው ከሆነ መልሱ ወደ አዲስ አበባ ይመልስዎታል፡፡
ፍሬሽወይን እንድሪስ ትባላለች፡፡ በታሪካዊው እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኤስቴቲክስ ስልጠና ዘርፍ የስነ-ውበት ሠልጣኝ ናት፡፡ ባለፈው ዓመተት በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ በተካሄደው የሰዓሊያን ውድድር ላይ ተካፍላለች፡፡
በዚህም በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ 25 ተወዳዳሪዎች መካከል 1ኛ በመውጣት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች፡፡ እንሆ ዛሬ አሸናፊ የሆነችበት የጥበብ ሥራዋ የሁለቱ ከተሞችን አስተሳስሮ በላይፕዚግ ከተማ በኩራት ለመቆም ችሏል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፍሬሽወይን እንድሪስን ሥራዋ ከፍ ባለ ደረጃ በመቀመጡ እንኳን ደስ ያለሽ ለማለት ይወዳል።
በክህሎት ልማቱ ላይ እየሰጡት ላለው ቁርጠኛ አመራር ለውጥ እያመጡ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን፣ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮን እንዲሁም የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክን ኮሌጅ አመራርና ባለሙያዎች በሙሉ ምስጋና ይገባቹኋል፡፡

Read More »
News

የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶችና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶችና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ማሰልጠን ፣ መሸለምና ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ የብሩህ -ኢትዮጵያ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በይፋ አስጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶችንና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡
በውድድሩ ከመላ ኢትዮጵያ በየደረጃው በተካሄዱ ውድድሮች አሸናፊ የሆኑ 150 ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪዎቹ የኢትዮጵያ ተስፋዎች ናቸው ብለዋል፡፡
የብሩህ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በየዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትሯ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮም የውድድሩን ተደራሽነት በመላ ኢትዮጵያ የማስፋት ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
የንግድ ፈጠራ ሃሳብን ጨምሮ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባካሄዳቸው የተለያዩ ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ወደ ምርት ገብተው የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈቱ የሚያስችል አዲስ ፕሮግራም ዕውን መደረጉንም ክብርት ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡
ከ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በልዩ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶችንና ቴክኖሎጂስቶችን በአንድ ማዕከል በማሰባስብ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን የማሻሻል ብሎም ቴክኖሎጂዎቻቸውን ወደ ሰፊ ምርት የማስገባት ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም አስረድተዋል፡፡
በፕሮግራሙ አንድ ዓመት ቆይታ አዳዲስ ተሞክሮዎች የተገኙበትና የሥራ ፈጣሪዎቾች ሃሳብ ወደ ፍሬ የተቀየረበት እንደነበረም ክብርት ሚኒስትር አመላክተዋል፡፡

Read More »
News

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከስልጠና ባለፈ ተልዕኳቸው ተጨባጭ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተጠቆመ

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከስልጠና ባለፈ ተልዕኳቸው ተጨባጭ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተጠቆመ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በምህንድስና ልህቀት ማዕከል እየተሰሩ ያሉ የውጭ ምርት መተካት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ያሉበትን ደረጃ እንዲሁም ሚኒስቴሩ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላስገነባቸው ቤቶች የሚሆኑ የቤት ቁሳቁሶች ዝግጅትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በዚህም ሥራው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ክብርት ሚኒስትር በዘርፉ የተደረገው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ያመጣውን ውጤት ማሳያም እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከሥልጠና ባለፈው ተልዕኳቸው የሥልጠና ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው የአካባቢያቸውን ችግር እየፈቱ የውስጥ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ እና የውጭ ምርቶችን ሊተኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን እየሰሩ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ መደረጉንም ክብርት ሚነስትር አንስተዋል፡፡
ይህም ተጨባጭ ውጤት እየተገኘበት ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር በክረምት በጎ ፈቃድ ለተገነቡት ቤቶች የሚሆኑ ግብዓቶችን በአጭር ጊዜ በጥራት እያመረቱ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

Read More »
News

ለሥራና ክህሎት እንዲሁም ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የ “Public Entrepreneurship and Innovation” ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

ለሥራና ክህሎት እንዲሁም ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የ “Public Entrepreneurship and Innovation” ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::
ለሚኒስቴሩ ተጠሪ በሆነው የኢትዮጵያ ኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲቲዩት (EDI) እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠና በህዝብ አገልግሎት ዘርፍ የፈጠራ፣ የትብብር እና የለውጥ ተግባራትን የማዳበር ዓላማ ያለው ነው።
ስልጠናው ፈጠራና ፍጥነት በታከለበት አግባብ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የተቀመጡ ግቦችን ስኬት ማላቅ የሚያስችል ሲሆን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ የተወጣጡ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
tigTIG
Scroll to Top