Mols.gov.et

bini

News

ኢንስቲትዩቱ ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀመረ

ኢንስቲትዩቱ ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀመረ
የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ያቋቋመውን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ሥራ አስጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድርን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት የቴክኒክና ሚያ ሥርዓቱን አካታች ማድረግ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ውስጥ ሁሉም ዜጎች ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ሥራ ያስጀመርነው ይህ ማዕከል ኢንስቲትዩቱ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሥልጠና ማዕከል ለመሆን ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ እንደሆነም ገልፀዋል።
በኢንስቲትዩቱ ውስጥ አካል ጉዳተኝነት ከውጤታማነት ያላገዳቸው አሠልጣኞች፣ ተመራማሪዎች እና ቴክኖሎጂስቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡
በትምህርትና ሥልጠናው መስክ ማዕከሉ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ከሌሎች ልምድና ተሞክሮዎችን የሚቀስሙበት ቦታም እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከልና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከልና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለዜጎች ሰፊ ሥራ ዕድልን ለመፍጠር በሚያስችሉ አማራጮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት ዲጂታል ኢኮኖሚን በመጠቀም ዘላቂ ልማትንና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ሀገራችን ‹‹ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025›› ግብን ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል፡፡
የዲጂታላይዜሽን ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የዜጎችን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት ያለውን አስተዋፅኦ መነሻ በማድረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዲጂታል ኢንተርፕሪነርሺፕ እንቅስቃሴን መጀመሩን የገለፁት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባለማው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት ቁጥራቸው ከ26ሺ ለሚልቁ ዜጎች የርቀት ሥራ(remote job) መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2023 የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰዎች ከሀገራቸው ሳይወጡ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የሥራ መስኮች ላይ መሰማራት በሚያስችለው የአውትሶርሲንግ ቢዝነስ ከ1.2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ መንቀሳቀሱ ዘርፉ ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ያለውን አቅም የሚያመላክት መሆኑም ተብራርቷል፡፡
ዘርፉ አዲስ እንደመሆኑ በሚጠበቀው ደረጃ ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና የአሠራር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ምህዳሩን ምቹ ከማድረግ አንፃር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ ኢንተርፕረነሮችና ወጣቶችን ከአሠሪዎች የሚያግናኙ የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም አልሚዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በጊግ ኢኮኖሚ የቁርጥ ሥራ እና ፍሪላንሲንግ ኢንዱስትሪ ላይ በሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከልን ጎበኙ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከልን ጎበኙ
የክህሎት ልማት ሥራችን በሥራ ገበያው ፍላጎት ጀምሮ በሙያ ብቃት ምዘና የሚጠቃለል ነው፡፡
በመሆኑም ከክህሎት ስልጠናው ባልተናነሰ መልኩ ወደ ሥራ ገበያው የሚቀላቀለው የሰው ሃይል ብቃቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የምዘና ስርዓቱ ወቅቱን በዋጀ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ እና ቀጣሪ ድርጅቶችም ለሚሰጠው የምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ዋጋ እንዲሰጡት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያውን ለመጠቀም በምናደርገው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ተቋማት የሚሰጡት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ወሳኝ በመሆኑ እነዚህ ተቋማት ለዜጎቻችን ተደራሽ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በዚህም ቪዥነሪ የምዘናና ሥልጠና ማዕከል ዓለም አቀፍ እውቅና ካላቸው የምዘና ተቋማት ጋር በመተባበር የከፈተውን የምዘና ማዕከል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጎብኝተዋል፡፡
ከማዕከሉ የሥራ አመራሮች ጋር በምዘና፣ ስልጠናና እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያም ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ ማዕከሉ በዚህ መልኩ ሥራ መጀመሩ በውጭ ሀገር ያሉ የሥራ ዕድሎችን ከማስፋት ባሻገር በትምህርትና ሥልጠናው መስክ ሙያዊ እድገትንና የዕድሜ ልክ ትምህርትን የሚያበረታታ እንዲሁም እንደ ሀገር ያለንን ተወዳዳሪነትን የሚጨምር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በመስኩ የግሉ ዘርፍ ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል::

Read More »
News

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ
በህዳር ወር የሚከበሩት የሴቶችና የህጻናት፣ የአረጋውያን እና የኤች አይቪ ኤድስ ቀን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተከብሯል፡፡
በመድረኩ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሐንስ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶችና ህጻናት ከሃገሪቱ ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ገልጸው በእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ከግለሰብ ጀምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየደረጃው በጋራ መቆም ይገባል፡፡
አካል ጉዳተኞች ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው እንዲጠቀሙ ማገዝ፣ የክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻል እና የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ኤች አይቪ ኤድስ አምራች ዜጎችን እየቀጠፈ የሚገኝ በመሆኑ ከመዘናጋት መውጣት እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ክቡር ጆሿ ታባህ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሄዱ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ክቡር ጆሿ ታባህ ጋር ውጤታማ ውይይት አካሄዱ።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ ያከናወነችውን ሪፎርም በዝርዝር ተመልክተዋል።
በዚህም ካናዳ ክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራን ጨምሮ በቀጣይ በሚለዩ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠውልኛል ብለዋል ክብርት ሙፈሪሃት ፡፡
ኢትዮጵያ እና ካናዳ ከግማሽ ምዕተ ዓመት የተሻገረ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በዘርፉ የሚደረገው ትብብርም ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ክቡር ጆሿ ታባህ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በትብብር ለመስራት ላሳዩት ቀርጠኝነት ከብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Read More »
News

ኢኮኖሚያዋና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል:: ክብርት አለሚቱ ኡመድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር

ኢኮኖሚያዋና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል::
ክብርት አለሚቱ ኡመድ
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጋምቤላ ክልል ጋር በመተባበር ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳር ግንባታ ላይ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ- መስተዳድር ክብርት አለሚቱ ኡሞድ በመድረኩ ላይ ባስተላለፊት መልዕክት፤ መንግስት የሥራ ዕድል ፈጠራውን ለማበረታታት በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።
በዚህም ተጨባጭ ውጤት እየታየ ቢሆንም ከሚፈለገው አንፃር ግን በዘርፉ ብዙ እንድንሰራ ይተበቃል።
ኢኮኖሚያዋና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና ይጫወታል::
ስለሆነም በመስኩ የሚታየውን ውስንነት ለመሻገር አመራሩ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይኖርበታል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፣ በክልሉ የተጀመረው የሰላም ግንባታ ሂደት ዘላቂ እንዲሆን ጠንካራ በሆነ የልማት ሥራዎች መታገዝ ይኖርበታል።
የሚሰጠው የፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሺፕ እና የኢኖቬሽን ሥነ ምህዳር ግንባታ ስልጠና ክልሉ ያለውን የልማት ፀጋ በሙሉ አሟጦ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም የአመራሩ ሚና እና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር ሁሉም ይህንን በመገንዘብ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

Read More »
News

ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ቀዳሚው ትኩረት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ

ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ቀዳሚው ትኩረት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አሰራሮችና አተገባበር ዙሪያ ከሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ሥራ አስኪያጆች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች የተካፈሉ ሲሆን በዘርፉ የአሰራር ስርዓት፣ በአፈጻጸም ላይ በሚታዩ ችግሮች፣ በመደበኛ ቁጥጥር እና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በዝርዝር ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ቀዳሚው ትኩረት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ ኤጀንሲዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የአሰራር ስርዓት ተጠቅመው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡
ይህንን የማይከተሉ ኤጀንሲዎች ላይ መንግስት አስፈላጊ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

ማኅበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችን የፈጠነ እንዲሆን የሚያደርግ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ማኅበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችን የፈጠነ እንዲሆን የሚያደርግ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በየደረጃው ለሚያካሂደው የማህበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት ለአዲስ አበባ አስተዳደር የአመቻችነት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡
በሥልጠና ማስጀመሪያው መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፣ ማኅበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት የሥራ ባህላችንን በማሳደግ፣ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን አሟጦ በመጠቀም የማህበረሰባችንን እሴት የማከልና የመፍጠር አቅምን ለማውጣት ያለመ ነው፡፡
ይህም ዜጎች አካባቢያቸውን እና የልማት ፀጋዎቻቸውን እንዲያስተውሉ፣ በችሎታቸው እንዲተማመኑና የማድረግ አቅማቸውን ከማሳደግ ባሻገር የቤተሰብን፣ የግለሰብንና የማህበረሰብን ምርታማነት የምናሳድግበት የለውጥ መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡
ሂደቱ በየአካባው ያሉ ችግሮችን በመለየት ወደ መልካም አጋጣሚነት መቀየርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ መነሻነት እያንዳንዱ አካባቢ ፀጋውን መሰረት ያደረገ የራሱ መለያ የሚሆን ምርት ማውጣት እንደሚጠበቅበትም አመላክተዋል፡፡
ውይይቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችን ያጠረና የፈጠነ፤ ፈጠራን ያከለና ያማከለ እንዲሆን እንደሚያደርግም ጨምረው ገልጽዋል፡፡
በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ በበኩላቸው፤ ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የሥራ ባህልን ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
tigTIG
Scroll to Top