Mols.gov.et

bini

News

ባለፉት 6 ወራት ከ 1.4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከክልልና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ2015 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ አካሄዷል፡፡
በመድረኩ ባለፉት 6 ወራት 1.8 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ የዕቅዱን 81 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ55 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተገለፀው፡፡
የሥራ ዕድሉ የተፈጠረዉም 70 በመቶ ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም እና 30 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ በቅጥር መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ከክህሎት ልማት አኳያም ነባር የሙያ ደረጃዎችን የመከለስና አዳስ የማዘጋጀት፣ አዲስ የምዘና መሳሪያዎች እና ተጨማሪ ቨርሽን፣ የስርዓተ ስልጠና እንዲሁም የማሰልጠኛ መሳሪያዎች የማዘጋጀት ሥራዎች በትኩረት መከናወናቸው ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በፌዴራል 5 እንዲሁም በክልሎች 525 ድርጅቶች ላይ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ሥራ አመራር ሥርዓት ለመዘርጋት ታቅዶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን የዕቅዱን 95 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ ነው የተጠቆመው።
ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያም ስርዓቱን ቀልጣፋ፤ ውጤታማ፣ የዜጎችን ክብር አስጠብቆ የስራ ዕድል ለመፍጠር ከመዳረሻ ሀገራት ጋር ሁለትዮሽ ስምመነት መፍጠር ላይ ሲሰራ የቆየ 77 የሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጀችን ለስራ ዝግጁ ማድረግ የተቻለ ሲሆን የስርዓተ ስልጠና ክለሳ እና የማሰልጠኛ መሳሪያ ዝግጅትም እንደተከናወነ ነው በመድረኩ የተገለፀው።

Read More »
News

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየዘረጋ መሆኑ ተጠቆመ።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየዘረጋ መሆኑ ተጠቆመ።

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ምክክርና ጉብኝት አካሂደዋል።

አምሳደሮቹ በተቋሙ መሰረታዊና ለውጥ አምጪ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ የዜጐችን ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

በመድረኩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሥራ ገበያውን መሰረት አድርጎ የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች የሚስተናገዱበት አሠራር እየተዘረጋ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጠቁመዋል።

Read More »
News

”በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

”በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል”
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

በዘርፉ ተወጥነዉ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እሳቤዎች ላይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሠው ሃብት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ዕድሎችና ፈተኛዎችን በመለየት ፈተናዎቹ ወደ ዕድል፤ ዕድሎችን ደግሞ ለመጠቀምና ወደ ዉጤት ለመቀየር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዘርፉን ስራዎች ግብ እንዲመቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

Read More »
News

ስምምነቱ የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የመመህራን አቅም በማጎልበት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

ስምምነቱ የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እና የመመህራን አቅም በማጎልበት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር)
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከቻይና አፍሪካ የሙያ ትምህርት ትብብር( CHINA-AFRICA VOCATIONAL EDUCATION ALLIANCE) ጋር የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ማላቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ፊርማ ተፈራርመዋል፡፡

የስምምነት ሰነድ ፊርማ የተፈራረሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) እና የቻይና አፍሪካ የሙያና ትምህርት ትብብርን ወክለዉ ማርክ ጎንግ(ዶ/ር) ናቸዉ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በፊርማ ስነ-ስራት ወቅት፤ ስምምነቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያለዉን ትብብር ይበልጥ የሚያሳድግ እና በጋራ አብሮ መስራት ያሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቻይና መንግስት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሰፊ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ይህ ስምምነትም የቴክክና ሙያ ስልጠና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የመመህራን አቅም በማጎልበት፣ የ 21ኛዉ ክፍለ ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልምድ መለዋወጥ እና በሌሎችም ዘርፎች አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የቻይና አፍሪካ የሙያ ትምህርት ትብብርን ወክለዉ ንግግር ያደረጉ ማርክ ጎንግ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ ቻይና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና በእጅጉ መጠቀሟን ገልጸዉ ልምዷን ደግሞ ለኢትዮጵያ ለማካፈል እና በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
ጥር 8/2015 ፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡
ለወቅታዊን ትኩስ የሥራና ክህሎት መረጃዎች
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols በመወዳጀት ይከታተሉን::

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
tigTIG
Scroll to Top