Mols.gov.et

ኢንስቲትዩቱ ታላቅ ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤና የቴክኖሎጂ ውድድር ሊያካሂድ ነው

June 11, 2026
ኢንስቲትዩቱ ታላቅ ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤና የቴክኖሎጂ ውድድር ሊያካሂድ ነው የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት (FDRE TVTI) ከሰኔ 5 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ታላቅ ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ እና የቴክኖሎጂ ውድድር እንደሚያካሂድ አስታወቀ። የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ዛሬ ለተለያዩ ሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንሱ ዋና ዓላማ በኢኒስቲትውቱ የምርምርና ቴክኖሎጂ ስራዎችን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ማሳደግ፣ የልምድ ልውውጥ ማካሄድ፣ እንዲሁም በተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችና የልማት አጋሮች መካከል ያለውን ቅንጅትና አጋርነት ማጠናከር ነው። ዘንድሮ የሚካሄደው ይህ ታላቅ ጉባኤ፦ “Future-Ready TVET and Technological Innovation for Sustainable Industrial Transformation” ወይም “መጻኢ የክህሎት ልማትና ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራን ያቀፈ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር” በሚል መሪ ሐሳብ እንዳለው ተገልጿል፡፡ ኮንፍረንሱ በዲጂታል ሽግግር እና የቴቬት ፈጠራኢንዱስትሪያል ለውጥ፣ በፈጠራ እና አረንጓዴ ሥርዓቶች፣በፖሊሲና አስተዳደር አካታችነት እና ዓለም አቀፍ አጋርነት ላይ አተኩሮ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል፡፡ በውድድሩ ላይ የሚቀርቡት የቴክኖሎጂ ስራዎችም በICT እና ዲጂታል ፈጠራ (AI, IoT, Cybersecurity)፣ በግብርናና አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ በላቀ ማኑፋክቸሪንግ፣ በታዳሽ ኃይልና አረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በግንባታና ዝቅተኛ ወጪ መኖሪያ ቤቶች ዘርፍ የተከፋፈሉ መሆናቸው ተገልጿል። ላፉት ስድስት ወራት በተጠናከረ ሁኔታ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ይህ ኮንፈረንስ እጅግ ሰፊ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከጀርመን፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ቱርክ፣ ኢራን፣ ማላዊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ጨምሮ ከ16 አገራት የተውጣጡ ተመራማሪዎችና ተወዳዳሪዎች ይሳተፉበታል። በጉባኤው ላይ ከ90 በላይ የምርምር ጽሑፎች እና ከ100 በላይ የቴክኖሎጂ/ፈጠራ ፕሮጀክቶች ከተመራማሪዎችና ባለሙያዎች የቀረቡ ሲሆን፤ በጥብቅ የሳይንሳዊ ግምገማ ሂደት ያለፉ 30 ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የምርምር ጽሑፎች እና 34 የተመረጡ የቴክኖሎጂ ስራዎች ለቀራቢነትና ለውድድር በብቃት ማለፋቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። በኮንፈረንሱ ላይ ኢንዱስትሪዎች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ የመንግስት ተቋማት፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የፈጠራ ባለቤቶች እና ፖሊሲ አውጪዎች በጋራ ይሳተፋሉ።
somSOM
Scroll to Top