Mols.gov.et

ሉሲ ገበያ- የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ምህዳር የማስፋት ጅምር

June 11, 2026
ሉሲ ገበያ- የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ምህዳር የማስፋት ጅምር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአገር በቀል ኢንተርፕራይዞችን የንግድ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥና የገበያ መሰረተ ልማትን ለማስፋት፣ በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በኩል ያበለጸገው «ሉሲ ዲጂታል ገበያ» (Lucy Digital Market) ወደ ሥራ መግባቱ ይታወቃል። ይህንን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ወደ መሬት ለማውረድና የፕላትፎርሙን አጠቃቀም ለማስፋፋት፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሥራና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት ከ119 ወረዳዎች ለተውጣጡ የገበያ እና ፕሮሞሽን ባለሙያዎች እና ከ15 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለተመረጡ ሰልጣኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል። ስልጠናው በዋናነት በኢ-ኮሜርስ (e-Commerce)፣ በሶሻል ሚዲያ ማርኬቲንግ፣ በዲጂታል ኮሙዩኒኬሽን እና የሉሲ ፕላትፎርም አጠቃቀም በመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አተኩሮ እየተሰጠ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የገበያ ጥናትና ትስስር ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በመድረኩ እንደገለጹት ስልጠናው ሲጠናቀቅ እያንዳንዱ ባለሙያ ቢያንስ የ20 ኢንተርፕራይዞችን ምርትና አገልግሎት ወደ ስራ በማስገባት፣ በቀጣይ 3 ወራት በአጠቃላይ ከ3 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ዲጂታል የገበያ ትስስሩ ለማስገባት ግብ ተቀምጧል። አክለውም ይህ ንቅናቄ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ዓለም ለማሻገር እና የገበያ ተደራሽነታቸውን ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
somSOM
Scroll to Top