Mols.gov.et

ብቁ የሰው ኃይል በስፋት በማፍራት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን የማድረግ ጉዞ

March 11, 2026
ብቁ የሰው ኃይል በስፋት በማፍራት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን የማድረግ ጉዞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የአሰሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በተደራጀ መልኩ የሠለጠነ እና ብቃት ያለዉን የሰዉ ሃይል ለመንግስት ተቋማትና ለድርጅቶች ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ለሀገር ዉስጥ ሥራና ሠራተኛ ኤጀንሲዎችና ለሴክተር መዋቅር ፈጻሚዎች በብሔራዊ የሥራ ስምሪት ፖሊሲና ስትራቴጂ ፣ በአዲሱ የሥራና ክህሎት እሳቤ፣ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ፣ ደንብ እና መመሪያ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል። በመድረኩ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ምክትል ሃላፊና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዮት ሸጋ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ አሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲዎች ለመንግስት ተቋማትና ለድርጅቶች የሚያቀርቡት የሰው ኃይል ብቁ፣ ተወዳዳሪና፣ በሥነ ምግባር የታነፀ እንዲሆን ለማስቻል ኤጀንሲዎቹ ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ቢሮዉ አዲሱን የዘርፉን እሳቤ መሠረት ባደረገ መልኩ ዜጎችን በስልጠና የማብቃትና መዝኖ ብቃታቸውን የማረጋገጥ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ዘገባ ያመላክታል፡፡ ብቁ የሰው ኃይል በስፋት በማፍራት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን የማድረግ ራዕይን የሰነቀው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በማንኛውም የሥራ መስክ ላይ የሚሰማሩ ዜጎች መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ስልጠናዎች ራሳቸውን እንዲያበቁ፣ ተመዝነው ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል ሥርዓት ዘርግቷል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሀገር ወዳድ፣ በሙያ ሥነ ምግባር የታነፀና በተሰማራበት መስክ ሁሉ ውጤታማ የሆነ ብቁ የሰው ኃይልን ለማፍራት የሚያስችል አዲስ የሪፎርም እሳቤን በመቅረፅም ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
somSOM
Scroll to Top