Mols.gov.et

🔊🚨አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት‼️

January 21, 2026
🔊🚨አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት‼️ ይህ ከስር የምትመለከቱት ቻናል የሥራና ክህሎት ቴሌግራም ቻናል አይደለም! 👇 🚨 https://t.me/fdre_mols የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አይደለም! 🚨 አሁኑኑ unfollow በማድረግ ራስዎን፣ ቤተሰብዎንና ዜጎችን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ! ትክክለኛው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡- ✅ https://t.me/FDRE_MoLSofficial ⚠️ ጥንቃቄ በአሁኑ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ስምና አርማ (Logo) በመጠቀም፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያወጣቸውን መረጃዎች በማባዛትና በማስመሰል የሚንቀሳቀሱ በርካታ ሀሰተኛ የቴሌግራም ገጾች እንዳሉ ደርሰንበታል። እነዚህ አጭበርባሪ አካላት ተገልጋዮችን የሚያታልሉባቸው መንገዶች፦ 👉የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ሽፋን በማድረግ በውስጥ መስመር (Inbox) ያነጋግሩዎታል፣ 👉ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደተደወለ በማስመሰል ያልተገባ የገንዘብ ክፍያ ይጠይቃሉ፣ 👉የተለያዩ የሐሰት ተስፋዎችን በመስጠት ንፁሃን ዜጎችን ለከፍተኛ ምዝበራ እየዳረጉ ይገኛሉ፣ ትክክለኛውን ገጽ እንዴት መለየት ይቻላል? የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋዊ ገጽ የሚከተሉት መለያዎች አሉት፦ ✅ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት (Verified Badge) ያለው ነው፣ ✅ከ 47 ሺህ በላይ ተከታዮች አሉት፣ ✅ማንኛውም ይፋዊ መረጃ በድረ-ገጻችንና በሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ላይ ከሰፈሩት አድራሻዎች ጋር የተናበበ ነው፣ 🛡 ሌሎችንም ይታደጉ 👉መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ፣ 👉በስህተት ሀሰተኛ ገጾችን እየተከታተላችሁ ያላችሁ ተገልጋዮች፣ በአስቸኳይ ከገጾቹ በመውጣት (Unfollow በማድረግ) ራሳችሁንና ወገኖቻችሁን ከማጭበርበር ይታደጉ፣ 👉መሰል አጭበርባሪ ቻናሎች ካጋጠምዎ መረጃውን ያድርሱን! ✅ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ሁልጊዜ ይፋዊ ገጾቻችንን ብቻ ይከታተሉ! ጥር 12/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
somSOM
Scroll to Top